‘አለቃ’ ልደቱ (ኢዴፓ)ና ኢህአዴግ በአንድነት ፓርቲ ላይ አዲስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጀመሩ – ‘ዘመቻ ቅጥፈት’ በአይጋ ፎረም ‘የትግል ሜዳ’

October 24th, 2008 Print Print Email Email

mushe_lidetu.gif (more…)

mushe_lidetu.gif

Click Here for the PDF Version


አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ በቅርቡ ህጋዊ ሰውነትን በማግኘት እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል። ፓርቲው በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ አመታዊ እቅዱንና በጀቱን ለህዝብ ይፋ አድርጎ፤ ባወጣው እቅድ አግባብ እተንቀሳቀሰ ነው። በእቅዱ መሰረት በሀገሪቱ ሁሉም ግዛቶች 117 ፅህፈት ቤቶችን የሚከፍት ሲሆን አመታዊ በጀቱም 7.3 ሚሊዮን ብር ነው። በዚሁም መሰረት፤ በወ/ሪት ብርቱካን የተመራው የመጀመርያው ቡድን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በማቅናት በደሴ ፅ/ቤት ከመክፈት ባሻገር ከአባላት ጋር በመወያየት አመራሮች ሲመረጡም በታዛቢነት ተገኝቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የአንድነት ፓርቲ ጅምር እንቅስቃሴ ያሰጋው ‘አለቃ’ ልደቱ ከ‘የእንጀራ አባቱ’ ኢህአዴግ ጋር በመሆን አዲስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍቷል። ታዛቢዎች “ዘመቻ ቅጥፈት” ብለው የሰየሙት ዘመቻ የተጀመረው በ‘አይጋ ፎረም የትግል ሜዳ’ ላይ ነው።

አይጋ ፎረም የተሰኘው የኢህአዴግ ድህረ-ገጽ ዛሬ ኦክቶበር 24 2008 ከ’አንባቢዬ’ ተላከ ያለውን ፅሁፍ አውጥቷል። ፅሁፉ ሁለት መሰረታዊ ግድፈቶች አሉት። የመጀመርያው ስህተት የይዘት ስህተት ነው። በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት መሰረት የፓርላማ አባላት በቡድን በመደራጀት (Caucusing) ሀሳባቸውንና አቋማቸውን የመግለፅ መብት አላቸው። አንድነት ፓርቲም ይህንን ተመርኩዞ ፓርላማ ያሉት አባላቶቹ በአንድነት ፓርቲ ስም እንዲደራጁ ጠይቋል። ‘አለቃ’ ልደቱ፤ ኢህአዴግና አይጋ ፎረም ይህንን ህገ-መንግስታዊ መብት አይቀበሉም።

ሁለተኛው የፅሁፉ መሰረታዊ ስህተት፤ ‘ቅጥፈት’ መሆኑ ነው። ደርቤ ንጉሴ ከመርካቶ በሚል የወጣው ፅሁፍ፤ በርግጥ የተላከው ከአቶ ሙሴ ሸሙ ነው። ይህንንም ለማወቅ፤ አይጋ ፎረም ድህረ-ገፅ ይሂዱ፤ ፅሁፉን ይክፈቱት፤ ፋይል የሚለውን ይጫኑ፤ ፕሮፐርቲስን ይጫኑ፤ የፅሁፉ ባለቤት የ’አለቃ’ ልደቱ አፈ-ቀላጤ አቶ ሙሴ ሸሙ መሆኑን እዛ ላይ ያገኙታል።

Comments are closed.